አቶ ጥላሁን ከበደ በገዜ ጎፋ ወረዳ በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦችን አጽናኑ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በክልሉ ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰቦች በስፍራው ተገኝተው አጽናኑ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በተከሰተው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
በማቱሣላ ማቴዎስ እና መለስ ታደለ