የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የኢትዮጵያን የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ድርድር ሒደት እደግፋለሁ አለች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እያካሄደች የምትገኘውን የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት የድርድር ሒደት የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በቴክኒክ እንደምትደግፍ አስታውቃለች፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ የንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፥ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የኢኮኖሚ ሚኒስቴር የውጪ ንግድ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ተሃኒ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ፥ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በሚያድግበት አግባብ ላይ ፍሬያማ ምክክር መደረጉን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያካሄደች የሚገኘውን የዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት የድርድር ሒደት የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በቴክኒክ እንድምትደግፍ ሚኒስትር ዴዔታው ቃል መግባታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ለዚህም ዝርዝር የጋራ እቅድ መነደፉን ጠቁመው÷ቃል ስለተገባው የቴክኒክ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡