Fana: At a Speed of Life!

ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በተለያዩ ጉዳዮች በትብብርና በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ÷ዩኤስኤአይዲ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በመተግበር የሚያደርገው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይ በዋሽ ዘርፍ እና በከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ላይ ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

በቀጣይ በግጭት ምክንያት የውሃ መሰረተልማቶች በተጎዱባቸው አካባቢዎች የመልሶ ግንባታና የማጠናከር ስራ ላይ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በዩኤስኤአይዲ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችና በሌሎች አጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የትግበራ ድግግሞሽ እንዳይከሰት የመናበብና የማጣጣም ስራ እንዲሰራም አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

በትምህርት ተቋማትና በጤና ተቋማት ተተግብሮ ውጤታማ የሆነውን “የግድቤን በደጀ ኢኒሼቲቭ” ዩኤስኤአይዲ እንዲደግፍ ጥሪ ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የዩኤስኤአይዲ የኢኮኖሚ እድገትና ሪዚሊየንስ ክፍል ተወካይ ዳይሬክተር ማርክ ሄንደርሰን በበኩላቸው÷ በተቋማቸው የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችን ከሌሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ጋር የማናበብና የማጣጣም ስራ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ዩኤስኤአይዲ የሚገነባቸው የውሃ ተቋማት ዘላቂ አገልግሎት በሚሰጡበት ሁኔታ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.