Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ለ2017 በጀት ዓመት ከ40 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ከ40 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጽድቋል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ነው የ2017 በጀት ዓመት ጥቅል በጀት ላይ በመምከር በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው፡፡

የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ሃላፊ አብዲራህማን አህመድ የ2017 በጀት ዝርዝርና አመዳደብ ባቀረቡበት ወቅት÷የክልሉ በጀት ዋነኛ ምንጮች ከክልሉ ታክስና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች እና ከፌዴራል መንግሥት ድጋፍ የሚገኝ ነው ብለዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በበኩላቸው÷በጀቱ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለው አግባብ እና የታለመለት የልማት ግብ እንዲመታ ይሰራል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.