Fana: At a Speed of Life!

ሚሲዮኑና ዳያስፖራው ለኦሊምፒክ ቡድን አስፈላጊውን የሞራል ድጋፍ ጋር ያደርጋል ተባለ  

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ሚሲዮን እና ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን አስፈላጊውን የሞራል ድጋፍ ጋር ያደርጋል ተባለ።

በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የሚሳተፈው የመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን ፓሪስ ከተማ ገብቷል፡፡

40 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ልዑክ ዛሬ ማለዳ ፈረንሳይ ፓሪስ ሲገባ በፈረንሳይ የኢፌዴሪ ሚሲዮን እና ፈረንሳይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በመጀመሪያው ዙር ወደ ፓሪስ ያቀናው የኦሎምፒክ ቡድኑ በኦሊምፒክና በፓራሊምፒክ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ማካተቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም  የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የስራ አመራር ቦርድ፣ የተለያዩ ፌዴሬሽኖች አመራሮች፣ የክልሎች ቢሮ ኃላፊዎች፣ የውሃ ዋና ስፖርት ቡድን እና በተጠባባቂነት የተያዙት አትሌቶች በቡድኑ ውስጥ ይገኙበታል ተብሏል።

ኦሊምፒክ ቡድኑ ፓሪስ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ያደረገው ሚሲዮኑና ዳያስፖራው በውድድር ወቅትም በስፍራው በመገኘት የሞራል ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለጹን ከፈረንሳይ የኢትዮጵያ ሚሲዮን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

33ኛው የ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ በነገው እለት በይፋ ይጀመራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.