Fana: At a Speed of Life!

የኮሌራ በሽታ መንስዔ እና ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሌራ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በማስከትል በሰውነት ውስጥ የሚገኝን ፈሳሽ አሟጥጦ በማስወጣት፣ አቅምን በማዳክም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታ ነው።

ኮሌራ ቫይብሮ ኮሌራ በተባለ ተህዋስ አማካኝነት የሚመጣና አንጀትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን÷ በሽታዉ በተህዋሱ በተበከለ ምግብና ውኃ አማካኝነት የሚመጣ ነው።

የኮሌራ በሽታ የሰውነት ፈሳሽን በማሟጠጥና አቅም በማሳጣት ተገቢዉ ህክምና ካልተደረገ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

የበሽታዉ ምልክቶች አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት፣ራስ ምታት፣ የቆዳ መሸብሸብ ሲሆኑ÷ ምልክቶቹ የታዩበት ሰዉ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርበታል፡፡

ከንፁህ መጠጥ ዉኃ እጥረት ጋር ተያይዞ የአካባቢና የግል ንፅህናን ለመጠበቅ አስቸጋሪ በሆነባቸዉ ቦታዎች በሽታዉ የከፋ ጉዳት ያደርሳል።

በሽታው በንፅህና እና ጥንቃቄ ጉድለት ሰዎች ተፋፍገዉ በሚኖሩባቸዉ ቦታዎች የመዛመት ዕድሉም ከፍተኛ መሆኑን ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መፀዳጃ ቤት በአግባቡ በመጠቀም፣ ምግብን በሚገባ አብስሎ በመመገብ፣ ከመጸዳጃ ቤት መልስ፣ ምግብ ከማቅረብ በፊት፣ ከማዘጋጀት በፊት፣ ምግብ ከመመገብ በፊት፣ ሕጻናትን ካጸዳዱ በኋላ፣ ህጻናትን ጡት ከማጥባት በፊት፣ በበሽታዉ ለተያዙ ሰዎችን እንክብካቤ ካደረጉ በኋላ እጅን በውኃና በሳሙና አጥርቶ በመታጠብ የኮሌራ በሽታን መከላከል ይቻላል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.