Fana: At a Speed of Life!

ሜታ ኩባንያ በናይጄሪያ ህዝብ ቁጥር ልክ ቅጣት ተላለፈበት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያ በህዝብ ቁጥሯ ልክ የ220 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ሜታ ኩባንያ እንዲከፍል ማስጠንቀቂያ ሰጠች፡፡

በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ የአሜሪካውን ሜታ ኩባንያን የሀገር ውስጥ የመረጃ ጥበቃ እና የግል ምስጢር ጥበቃን ጥሰሃል ስትል ከሳዋለች፡፡

በዚህም የሜታ ኩባንያ ፖሊሲዎች የናይጄሪያ ተጠቃሚዎች የግል መረጃቸው ላይ ያላቸውን መብት ተጋፍቷል ስትል ነው ክሷን ያቀረበችው፡፡

በዚህም የፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ዋትስአፕ ባለቤት የሆነው ሜታ “ዋትስአፕን ለመቀላቀል ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመዘገቡ መረጃው ለጥናት እንዲጋራ ተስማምተዋል የሚል አምድ እንዳለ ደርሰንበታል“ ብለዋል አንድ የሀገሪቱ ባለስልጣን፡፡

ሜታ የግል ምስጢር ህጎችን በመጣሱ የ220 ሚሊየን ዶላር ቅጣት እንዲከፍል እና ለምርመራ ወጪ ተጨማሪ 35 ሺህ ዶላር እንዲከፍል የሀገሪቱ መንግስት የ60 ቀናት ጊዜ መስጠቱ ተነግሯል፡፡

ሆኖም ሜታ ለክሱ በይፋ ምላሽ አለመስጠቱም ተሰምቷል፡፡

ወደ 164 ሚሊየን የሚጠጉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ያላት ናይጄሪያ፥ ከ51 ሚሊየን በላይ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች እንዳሏት ባለፈው ዓመት ታሕሳስ ወር ላይ የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ገልጾ ነበር።

ሜታ መሰል ክስ ሲደርሰው የመጀመሪያው አለመሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፥ ቱርክ በቅርቡ በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ትሪድስ እና ዋትስአፕ ፕላትፎርሞች የመረጃ መጋራት ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ ኩባንያውን 37 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ቅጣት ማስተላለፏ ይታወሳል፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያም የአውሮፓ ህብረት ሜታን መክሰሱን አርቲ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.