Fana: At a Speed of Life!

“የትርክት ዕዳና በረከት” የተሰኘው የሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መፅሃፍ ተመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተፃፈው “የትርክት ዕዳና በረከት” መፅሐፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈው “የትርክት ዕዳና በረከት” መጽሐፍ ምረቃ ላይ ከታደሙ ግለሰቦች ለተነሱ ጥያቄዎች ደራሲው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም በውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸውን የኢትዮጵያን እውቀት እንዲማሩ ቢያደርጉ አሁን የምንጨቃጨቅበትን ጉዳዮች በንግግር መፍታት የሚያስችል እውቀት እንዳለን ይረዳሉ ብለዋል።

በሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በማብራሪያቸው ገበያው የሚፈልገውን ሳይሆን እውቀትን የምናወርስበት ጉዳይ ላይ ማተኮር አለበን ነው ያሉት።

በተለይም ምሁራን እውቀታቸውን በሃላፊነት እንዲያካፍሉም ምክረ ሀሳባቸውን መስጠታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከበፊት ጀምሮ የኛ መሰረታዊ ችግር አለመነጋገር ነው ያሉት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጠረጴዛ ዙሪያ ከተነጋገርን ብዙ ነገሮቻችን ቀላል ናቸው ሲሉም አስረድተዋል።

“የትርክት ዕዳና በረከት” መፅሐፍ በ46 ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን÷575 ገፆች ያሉት ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.