Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ በመሬት ናዳ አደጋው በበርካታ ዜጎች ሕይወት ላይ በደረሰው አስከፊ አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋው ምክንያት በበርካታ ዜጎች ሕይወት ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ገልፀዋል፡፡

ከንቲባዎቹ ለሟች ቤተሰቦች እና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን የተመኙ ሲሆን ÷ በቀጣይ ከክልሉ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.