Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጎርጎራ ሪዞርትን በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል ስር የማስተዳደር ኃላፊነትን ዛሬ በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በተደረገ የስምምነት ስነ-ስርዓት ተረክቧል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ሥራ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የተገነቡትን ሀላላ ኬላ ሪዞርት፣ የወንጪ ኢኮ ሎጅ እንዲሁም የጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅን የማስተዳደር ኃላፊነትን በቅርቡ ወስዶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.