በድጋፍ አሰባሰቡ ላይም ከ8 ሚሊየን 88 ሺህ በላይ መደበኛ ለጋሾች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡
የድጋፍ አሰባሰቡን ስኬታማነት ተከትሎ ከጀርባ የሕዝብ ድጋፍ እንዳለ እና ትራምፕም ይህንን እንደ ፈሩ የሃሪስ የዘመቻ ቃል አቀባይ ኬቨን ሙኖዝ ተናግረዋል፡፡
የሃሪስ የዘመቻ ቡድን በ24 ሰዓት ያሰባሰበው ገንዘብ እስከ አሁን በአሜሪካ ታሪክ የትኛውም ዕጩ አሰባስቦት እንደማያውቅም አረጋግጠዋል፡፡
በ24 ሰዓት ውስጥ የሃሪስ ቡድን 43 ሺህ አዳዲስ ለጋሾች መጨመሩን ጠቅሶ÷ ከለጋሾቹ መካከልም ከግማሽ የሚልቁት በየሣምንቱ ድጋፍ ለማድረግ መፈረማቸውን ኢንዲያ ቱዴይ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን ምክትላቸው ካማላ ሃሪስን በዕጩነት እንዲወዳደሩ የተኩት ከተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር ካደረጉት ደካማ የክርክር ሂደት በኋላ በፓርቲቸው ጭምር የደረሰባቸውን ከፍተኛ ጫና ተከትሎ መሆኑ ይታወሳል፡፡