Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረትና ፒፕል ኢን ኒድ በወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና ፒፕል ኢን ኒድ በኢትዮጵያ ወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ላይ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንደሚያጠናክሩ ገለጹ፡፡

ፒፕል ኢን ኒድ በኢትዮጵያ በርካታ ክፍተቶች በሚስተዋሉበት የቆዳ ኢንዱስትሪ ላይ በቴክኖሎጂ እና በክህሎት የታነጹ ሥራ ፈጠሪ ወጣቶችን ለማፍራት ፕሮጀክት ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ድርጅቱ ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በኦሮሚያ ክልል አዳማና ቢሾፍቱን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች በርካታ ወጣቶች በዘርፉ የስራ እድል እንዲፈጥሩ ማስቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ም በሞጆ እና አካባቢው ከሚገኙ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ተረፈ ምርቶችን ወደ ጠቃሚ ግብዓት እንዲቀይሩ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም ወጣቶች እና ሴቶች ያመረቷቸውን አዳዲስ ምርቶች ለገበያ ማቅረባቸውን የፒፕል ኢን ኒድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ክላራ ጄሊንኮቫ ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ በበኩሉ÷ በኢትዮጵያ ወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ፒፕል ኢን ኒድ በቆዳው ዘርፍ ወጣቶች የስራ አድል እንዲፍጥሩ እያከናወነ የሚገኘው ሥራ አበረታች እንደሆነ መገለጹንም የህብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.