ለፓሪስ ኦሊምፒክ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ትኬት ተሽጧል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ ኦሊምፒክ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ትኬት መሸጡን የዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ።
የኮሚቴው የስፖርቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ኪት ማክኮኔል እንደተናገሩ፤ ለኦሊምፒክ ጨዋታዎች የተሸጠው ትኬት ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው።
በፈረንሳይ ታሪክ የስፖርት ውድድር ላይ ለመታደም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ትኬት የተሸጠበት አጋጣሚ እንደሆነም ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም ለኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ትኬት የተሸጠው በፈረንጆቹ 1996 በተካሄደው የአትላንታ ኦሊምፒክ ሲሆን፤ በወቅቱም 8 ነጥብ 3 ሚሊየን ትኬት መሸጡን የስፑትኒክ ዘገባ አስታውሷል።
የኦሊምፒክ ጨዋታው በሚካሄድበት ወቅት ጸጥታ ማስጠበቅን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት 30 ሺህ ያህል ሰራተኞች መመደባቸውንም ተናግረዋል።
የፓሪስ ኢሊምፒክ በፈረንጆቹ ከሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2024 ድረስ እንደሚካሄድ ይታወቃል።