Fana: At a Speed of Life!

የፅንፈኛው ቡድን የሎጅስቲክስ አቅራቢውን ጨምሮ አዲስ ሲሰለጥኑ የነበሩ አባላቱ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሳል ወረዳ ለሚንቀሰቀሰው ፅንፈኛ ቡድን ሎጅስቲክስ አቅራቢ የነበረው ነጋ ፋንታሁንን ጨምሮ አዲስ ሰልጣኝ የቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ የኮማንዶ ሬጅመንት አስታወቀ፡፡

መነሻቸውን አዲስ አበባና ግሸን ከርቤ በማድረግ ለእኩይ አላማቸው የተሰበሰቡና ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ ሰልጣኞችና አሰልጣኞችን ጨምሮ በአርጎባ ማህበረሰብ ቃሉ ወረደ ድማ ቀበሌ ላይ እያሉ ከነግብረአበሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለፀው፡፡

እነዚህን አባላት በቁጥጥር ስር በማዋል በተሰራው ስራ የቃሉ ወረዳ የፅንፈኛው ቡድን ሃላፊ የነበረውን አብዱ መሃመድን ጨምሮ 16 የፅንፈኛው ሰልጣኞችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ነው የተባለው።

የህዝቡን ሠላም ለማደፍረስና የሠላሙ መረጋጋት እንዳይቀጥል ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ በቡድኑ አባላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት የቡድኑ አባላት በተሣሣተ መንገድ የሕዝቡን ሠላም ሲረብሹ መቆየታቸውንና አሁን ግን በፈፀሙት የሽብር ስራ መፀፀታቸውን ተናግረው ከዚህ በኃላ ከመንግሥት ጎን በመቆም ለሠላም እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.