Fana: At a Speed of Life!

የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ በመባሌ ትልቅ ክብር እና ምስጋና አለኝ-አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢ ኤ ስ ፒ ኤን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ በመባሌ ትልቅ ክብር እና ምስጋና አለኝ ሲል አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ገለፀ፡፡

ኢ ኤ ስ ፒ ኤን የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ 10 ታላላቅ አፍሪካውያን ስፖርተኞችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም የረጅም ርቀት ሯጩ አትሌት ቀነኒሳም ቀዳሚውን ደረጃ ይዟል፡፡

ይህን ተከትሎ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማህበራዊ ትስስር ገፁ 21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አትሌት ስለሆንኩኝ ትልቅ ክብር እና ምስጋና አለኝ ብሏል፡፡

በአትሌቲክስ የህይወት ጉዞዬ ለረዱኝ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን መግለጽ እፈልጋለሁም ነው ያለው፡፡

“በእኔ ስላመኑ እና አዲስ ከፍታ እንድደርስ ስላነሳሱኝ አድናቂዎቼን፣ ጓደኞቼን፣ ቤተሰቦቼን እና ደጋፊዎቼን አመሰግናለሁም “ብሏል አትሌቱ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.