Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት አጋጥሟታል – ኅብረቱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአኅጉሪቱ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት ማጋጠሙን የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት፣ የሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር መሐመድ ባልሆሲን በሰጡት መግለጫ፥ የመምህራን እጥረቱ በአኅጉሪቱ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የተቀመጠውን በትምህርት የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት አኅጉሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል።

የመምህራን እጥረቱን ለመሙላትና በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ኢንቨስት የሚደረገውን በአግባቡ ለመጠቀምም ጠንካራ ጥረቶች እንደሚያስፈልጉ አስረድተዋል፡፡

በአፍሪካ የመምህራን እጥረትን ለመፍታት፣ የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ 90 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡

በአፍሪካ ያለው የትምህርት ሥርዓት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.