Fana: At a Speed of Life!

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በዚሁ መሰረት የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን÷ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

ፈተና ከወሰዱ 85 ሺህ 46 በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 94 ነጥብ 3 በመቶ ያህሉ 50 በመቶ እና በላይ ማምጣታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

https://aa6.ministry.et/#/result ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.