Fana: At a Speed of Life!

የአሐዱ ባንክ አመራርና ሰራተኞች በእንጦጦ ተራራ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሐዱ ባንክ አመራርና ሰራተኞች በእንጦጦ ተራራ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

አሐዱ ባንክ በይፋ ሥራ የጀመረበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ማህበራዊ ተሳትፎ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ መሠረትም በዛሬው ዕለት የባንኩ አመራርና ሰራተኞች በእንጦጦ ተራራ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ሰፊአለም ሊበን በዚህ ወቅት እንዳሉት ፥ ችግኝ መትከል ከማህበራዊ ሃላፊነት ባለፈ የተፈጥሮ ሃብት ሚዛንን ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና አለው።

ባንኩ በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የተተከሉ ችግኞች በተገቢው ሁኔታ እንዲጸድቁም ባንኩ አስፈላጊውን እንክብካቤ ያደርጋል ነው ያለት።

ባንኩ በማህበራዊ ተሳትፎው የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመው ፥ በዚህም የደም ልገሳ እና እርዳታ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል።

አሐዱ ባንክ በተለያዩ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችና ማህበራዊ ተሳትፎዎች ሰራተኞችን እና አጋር አካላትን በማስተባበር የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.