Fana: At a Speed of Life!

ከ237 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ ተኪ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ237 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ተኪ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረቡን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተመረቱት ተኪ ምርቶች መካከልም÷ የቢራ ገብስ ብቅል እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግብዓት ዋነኞቹ መሆናቸው ተብራርቷል፡፡

በሌላ በኩል ከ124 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ ግብዓቶችን ለአምራቾች በማቅረብ የገበያ ትስስር ተፈጥሯል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶም ከ606 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.