Fana: At a Speed of Life!

የባርሴሎና ደጋፊዎች ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም በቲክቶክ ገንዘብ ማዋጣት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባርሴሎና ደጋፊዎች ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም በክለቡ ይፋዊ የቲክቶክ አካውንት ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸው ተገለፀ፡፡

የአትሌቲክ ቢልባኦ እግር ኳስ ክለብ ንብረት የሆነው የ22 ዓመቱ ኒኮ ዊሊያምስ የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊ በሆነው የስፔን ብሄራዊ ቡድን ስኬታማ ጊዜን ማሳለፉ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህም ወጣቱ የመስመር አጥዊ ኒኮ ዊሊያምስ የእንግሊዙን ቼልሲ ጨምሮ በባርሴሎና እና በበርካታ የአውሮፓ ክለቦች የዝውውር እይታ ውስጥ ገብቷል፡፡

ሮይተርስ በዛሬው እለት እንዳስነበበው በገንዘብ ቀውስ የሚገኘው የባርሴሎና ደጋፊዎች ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም በክለቡ ይፋዊ የቲክቶክ አካውንት ገንዘብ ማሰባሰብ ጀምረዋል፡፡

የካታላኑ ክለብ ደጋፊዎች ኒኮ ዊሊያምስ ልክ እንደ አውሮፓ ዋንጫው ሁሉ በባርሴሎና ቤት ከወጣቱ የፊት መስመር አጥቂ ላሚን ያማል ጋር እንዲጣመርላቸው እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ኒኮ ዊሊያምስ እና ላሚን ያማል በአውሮፓ ሻምፒዮኑ የስፔን ብሄራዊ ቡድን ደምቀው መታየት የቻሉ ሲሆን ከጨዋታ ውጭ በማህበራዊ ህይወታቸው የጠበቀ ጓደኝነት እንዳላቸው አሳይተዋል።

እንደ ትራንስፈር ማርኬት ዘገባ ከሆነ ኒኮ ዊሊያምስ አሁን ላይ የዝውውር ዋጋው 70 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 76 ነጥብ 29 ዶላር ይገመታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.