Fana: At a Speed of Life!

ኤጄንሲው 1 ሺህ ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሚግሬሽን ዜግነትና እና ወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ 1 ሺህ ሞተር ሳይክሎችን ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ማስረከቡን አስታውቋል።

ሞተር ሳይክሎቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ 102 ሚሊየን 524 ሺህ 400 ብር ድጋፍ እና ከመንግስት ከቀረጥ ነጻ በ56 ሚሊየን 38 ሺህ 156 ብር ብር የተገዙ መሆናቸው ተገልጿል።

ይህም በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ያለውን የወሳኝ ኩነት የምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

በተለይም በወረዳ ወሳኝ ኩነት ጽህፈት ቤቶች የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ያስችላሉ ነው የተባለው ።

በሀገሪቱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ዓለም አቀፍ መርሆዎችን በጠበቀ መልኩ በዜጎች ላይ የሚከሰቱ እንደ ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺ እና ሞት ወሳኝ ኩነቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ወጥቶ ስራ መጀመሩ ይታወቃል።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.