ኢትዮጵያና ጅቡቲ በወጪንግድ ያላቸውን ትብበር ለማጠናከር መከሩ On Jul 17, 2024 63 አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከጅቡቲ የንግድ ሚኒስትር ሙሃመድ ዋርሳማ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን የወጪ ንግድ ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ንግድ በሚሳለጥበት አግባብ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይም የንግድ ትስስር እና ቀጣናዊ ኢኮኖሚያዊ ውሕደትን ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ እንደሆነች አረጋግጠዋል፡፡ 63 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint