Fana: At a Speed of Life!

ሳውዝጌት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በራሳቸው ፈቃድ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ፡፡

ሳውዝ ጌት ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የእግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ከስምንት ዓመታት በኋላም በይፋ ከብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በቡድኑ በነበራቸው ቆይታም በ2024ቱ እና 2021ዱ የአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝን ለፍጻሜ ማድረስ ችለዋል፡፡

እንዲሁም በ2018 የዓለም ዋንጫ እስከ ግማሽ ፍፃሜ እና በ2022 የዓለም ዋንጫ ደግሞ እስከ ሩብ ፍፃሜ አድረሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ በቆይታቸው ዋንጫ ማሳካታ ባለመቻላቸው ትችት ሲሰነዘርባቸው ቆይቷል፡፡

በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ በስፔን 2 ለ 1 መረታቷ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.