Fana: At a Speed of Life!

የስክሪን ብርሃን ለልጆች አይን ጤንነት ያለው አሉታዊ ተፅዕኖ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን ላይ ልጆች ስክሪን ላይ (ስልክ፣ ቲሌቪዥን) የሚያሳልፉት ጊዜ በርከት እያለ መጥቷል፤ ይህ ደግሞ የልጆች የአይን ጤንነነት ላይ ጉዳት ያስከትላል።

በዚህም ወላጆች ልጆች ስክሪን የሚያዩበትን የቆይታ ጊዜ መወሰን ወይም መገደብ አለባቸው፡፡

የስክሪን ብርሃን የልጆች አይን ጤንነት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ምንድነው?

-ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ መሆን እና ሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር፡- ልጆች ስክሪን ላይ በሚቆዩበት ጊዜ ውጭ ወጥቶ የመጫወት አጋጣሚያቸው ይቀንሳል፤ ለዚህም ውጭ እንዲጫወቱ ማድረግ ከአካላዊ ጤናቸው ባለፈ ለአይን ጤንነትም ጉልህ ሚና ይጫወታል፡:

– የአይን መድከም፡- አይናችን እረፍት ይፈልጋል፤ ልጆች ደግሞ አንድ ነገር ሲይዙ ቶሎ ላይተዉ ስለሚችሉ ለብዙ ሰዓታት ስክሪን ላይ ሊቆዩ ይችላሉ፤ ይህም ከስክሪን የሚወጣው ብርሃን አይንን የበለጠ ያደክማል፡፡

– እንዲሁም ረጅም ሰዓት ስክሪን ላይ ማሳለፍ የአይን ድርቀት እና መቆጣትን ያስከትላል፡፡

-የአይን ትኩረትን ለመቀያየር መቸገር፡- አንድ ነገር ላይ ለረዥም ጊዜ አትኩሮ መቆየት እይታን አስተካክሎ ሌሎች ነገሮችን ለማየት በተለይ የርቀት እይታ ላይ ያስቸግራል፡፡

ይህ ጊዜያዊ ችግር ሲሆን በጥቂት ሰዓታት፣ ቀናት አሊያም ሳምንታት ወደ ቀድሞ እይታ እንደሚመለስ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

– ከእይታ በላይ እንቅልፍ ላይ ያለው ችግር፡- የእንቅልፍ ጊዜን መሻማት ሌላኛው ህፃናት ላይ የሚፈጥረው ችግር ነው፡፡

በዚህም ወላጆች ልጆች ስክሪን የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ፣ ውጪ እንዲጫወቱ ማበረታታት፣ ስልክ ወይም ታብሌት መጠቀም የማይችሉባቸውን ቦታዎች መለየትና በተለይ ከመኝታ በፊት መኝታ ቤት ውስጥ ስልክ እንዳይጠቀሙ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በዚህ ረገድ ወላጆች ለልጆች አርዓያ በመሆን እነርሱም ስልክ የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ አለባቸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.