Fana: At a Speed of Life!

አንሄል ዲ ማሪያ ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀቲናዊው የክንፍ መሥመር ተጫዋች አንሄል ዲ ማሪያ ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ዋንጫ (ኮፓ አሜሪካ) ድል ማግስት ከብሄራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

ባለፈው ህዳር ወር ከኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ በኋላ ከብሄራዊ ቡድኑ እንደሚለያይ አስታውቆ የነበረው የ36 ዓመቱ ዲ ማሪያ፤ ዛሬ ንጋት ላይ አርጀንቲና ኮሎምቢያን ላውታሮ ማርቲኔዝ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ካሸነፈች በኋላ ብሄራዊ ቡድኑን በይፋ ተሰናብቷል፡፡

ዲ ማሪያ በአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን 16 ዓመታትን ያሳለፈ ሲሆን በአራት የዓለም ዋንጫዎች እና የኮፓ አሜሪካ የውድድር መድረኮች ጋር ተሰልፎ መጫዎት ችሏል፡፡

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ በነበረው የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የነበረው ዲ ማሪያ በብሄራዊ ቡድኑ ስኬት ላይ የራሱን አሻራ አሳርፏል፡፡

የባለ ግራ እግር የክንፍ ተጫዋች ዲ ማሪያ ለአርጀቲና ብሄራዊ ቡድን በሁሉም የውድድር ዓይነቶች 144 ጊዜ ተሰልፎ 31 ጎሎችን ማስቆጠር መቻሉን ቢ ኢን ስፖርትስ አስነብቧል፡፡

ካስቆጠራቸው ጎሎች መካከልም በፈረንጆቹ 2021 አርጄንቲና ብራዚልን 1 ለ 0 አሸንፋ የኮፓአሜሪካ ዋንጫን ስታነሳ እንዲሁም፤ በኳታሩ ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ፈረንሳይ ላይ ያስቆጠራት አንድ ጎል ይጠቀሳሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.