የባለስልጣናት ቡድን የባለሀብቶችን ቡድን 2 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመቻል ስፖርት ቡድን 80ኛ ዓመት ምስረታ አከባበር በተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ የባለስልጣናት ቡድን የባለሀብቶችን ቡድን 2 ለ 1 አሸንፏል።
“መቻል ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ያለውን የመቻል ስፖርት ክለብ 80ኛ ዓመት ምስረታ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በባለሀብቶች መካከል የተካሄደው ወዳጅነት ጨዋታ ተጠናቅቋል።
በባለስልጣናቱ ቡድን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለን ጨምሮ ሌሎችም ተጫውተዋል።
በባለሃብቶች በኩል ደግሞ በላይነህ ክንዴን ጨምሮ ሌሎችም መሳተፋቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
ፖርቹጋላዊው ሉዊስ ናኒ እና ናይጀሪያዊው ንዋንኩ ካኑ በስታዲየሙ ተገኝተው ጨዋታውን ተመልክተዋል፡፡