Fana: At a Speed of Life!

ሊዊስ ናኒና ኑዋንኩ ካኑ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ኑዋንኩ ካኑ በኢትዮጵያ ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ስኬታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን አሉ።

ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ የገቡት የቀድሞ እግር ኳስ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ የዓመት ምስረታ በዓል ላይ እንዲገኙ በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

ፖርቹጋላዊው የቀድሞ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዊስ ናኒ÷ ኢትዮጵያ በመምጣቱ ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ፤ የኢትዮጵያን ባህልና ህዝቡን የመተዋወቅ ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል።

በመቻል ስፖርት ክለብ የምስረታ በዓል እንድገኝ ግብዣ ሲቀርብልኝ በደስታ ነው የተቀበልኩት ያለው ሊዊስ ናኒ፤ አጋጣሚው ኢትዮጵያን ለማየትና ለመጎብኘት ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልጿል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ እግር ኳስ ስፖርተኞችን ለማፍራት በወጣቶች አካዳሚ ላይ መሥራት ይገባል ነው ያለው፡፡

ናይጄሪያዊው የቀድሞ ተጫዋች ኑዋንኩ ካኑ በበኩሉ÷ፕሮፌሽናል ተጫዋች ለመሆን ህልም የሰነቁ አፍሪካውያን ወጣቶችና ታዳጊዎች ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብሏል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ እግር ኳስን ለማሳደግ በሚሰራው ስራ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።

ወደ ኢትዮጵያ የመጣንበት ዋና ዓላማ ወጣቶችና ታዳጊዎችን ለማበረታታት እና የበለጠ እንዲነቃቁ ለማድረግ ነው ብለዋል።

በእግር ኳስ ስኬታማ የሆኑ ተጫዋቾች እገዛ ያስፈልጋል እዚህ የተገኘነው በዛ መንፈስ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ሲሉም አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.