አቶ አህመድ ሽዴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ ከፈረንጆቹ ሐምሌ 22 እስከ 26 ቀን 2024 ድረስ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 4ኛው የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ የመጀመሪያ ዙር ዝግጅት አስመልክቶ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው የአፍሪካውያንን የጋራ ጥቅም እና የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭን በማጠናከር ላይ ትኩረቱን እንደሚደርግ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ከፈረንጆቹ መስከረም 4 እስከ 6 ቀን 2024 ድረስ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የአፍሪካ የከተሞች ፎረም ለማስተናገድ እየተዘጋጀች እንደምትገኝ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡