የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ካቢኔያቸውን በተኑ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሁለት ባለስልጣናት ውጪ ካቢኔያቸው መበተኑን አስታውቀዋል፡፡
ውሳኔው የተለያዩ የግብር ጭማሪዎችን በያዘው የፋይናንስ ረቂቅ ሕግ ላይ የተከሰተውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ የተወሰነ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
በዚህ መሰረትም ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የካቢኔያቸው ዋና ጸሃፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሪጋቲ ጋቻጓ በሃላፊነት ሲቆዩ ቀሪው ካቢኔያቸው ሙሉ በሙሉ መበተኑን አስታውቀዋል፡፡
በኬንያ አዲሱን የፋይናንስ ሕግ በመቃወም በሀገሪቱ በርካታ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ይታወቃል፡፡
ተቃውሞውን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የሀገሪቱ ዜጎች ላይ ግብር የሚጥለውን ሕግ መሰረዛቸው የሚታወስ ነው