Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የጤና አገልግሎት ጥራትን ለመጠበቅ የተሠራው የቁጥጥር ሥራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የጤና ተቋማት እና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለመጠበቅ የተሠራው የቁጥጥር ሥራ አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

በክልሉ በሀገር አቀፍ የጤና ተቋማትና አገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ምቹ የሕክምና ቦታ መያዝ፣ ለተቋም በቂ የግብዓት አቅርቦት ማሟላትና የባለሙያዎችን ብዛት መሰረት በማድረግ በየጊዜው በሚደረግ ቁጥጥር ለውጥ እየመጣ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተመረጡ ዋና ዋና ከተሞች ተቆጣጣሪዎችን በመመደብ ተቋማት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተሠራው ሥራ አበረታች መሆኑም የቢሮው የጤና እና ጤና ነክ ግብዓት ቁጥጥር ዳይሬክተር ጌትነት ስንታየሁ ገልጸዋል።

ባለፈው በጀት ዓመት የመድሐኒት ችርቻሮ ድርጅቶችን ጨምሮ 8 ሺህ 593 የግልና የመንግሥት የጤና ተቋማትን በመከታተል ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሐኒቶች መወገዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም 100 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ጊዜያቸው ያለፈና ስታንዳርዱን ያላሟሉ የምግብ አይነቶችን ማስወገድ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ከሆስፒታሎች እስከ መለስተኛ ክሊኒክና የመድሐኒት ችርቻሮ ተቋማት ድረስ አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ እስከ 10 ዓመት ጊዜ ተከማችተው የተቀመጡ መድሐኒቶችን ማስወገድ እንደተቻለም ተጠቅሷል፡፡

ከቁጥጥር ባለፈም ማኅበረሰቡ የመድሐኒቶችን የአገልግሎት ጊዜ አይቶ እንዲጠቀም ለማድረግ ግንዛቤን የማሳደግ ሥራ እየተሠራ ነው ተብሏል።

የመድሐኒት ብክነትን ለመቆጣጠር ተቋማት ከማከማቻ እስከ ተጠቃሚው ድረስ የተዋቀረ ወጥ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባቸውም ተመላክቷል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.