ከስፔን ጋር ለፍጻሜ የሚፋለመው ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ይለያል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከስፔን ጋር ለፍጻሜ የሚፋለመው ብሔራዊ ቡድን የሚለይበት የእንግሊዝና ኔዘርላንድስ (ሆላንድ) ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ሁለተኛ መርሐ-ግብር እንግሊዝ ከኔዘርላንድስ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ በሲግናል ኢዱና ፓርክ ስታዲየም የሚያደርጉት ብርቱ ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በሩብ ፍጻሜው እንግሊዝ ስዊዘርላንድን እንዲሁም ኔዘርላንድስ ቱርክን በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡
ትናንት በተካሄደው የመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ስፔን ፈረንሳይን 2 ለ 1 በመርታት ለፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያ ሀገር ሆናለች።
በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ እንግሊዝ 5ኛ እንዲሁም ኔዘርላንድስ 7ኛ ላይ ተቀምጠዋል።