Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወባ በሽታ ስርጭት እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወባ በሽታ ስርጭት እየጨመረ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

ቢሮው የወባ በሽታ ስርጭትን መከላከል የሚያስችል ክልላዊ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ አካሂዷል።

ባላፈው አንድ ሳምንት ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የገለጸው የክልሉ ጤና ቢሮ፤ አሁን ካለው ወቅታዊ የአየር ሁኔታ፣ የህብረተሰቡ ተገቢ ያልሆነ የአልጋ አጎበር አጠቃቀምና የጤና ኤክስትንሽን ስራ መዳከም የበሽታው ስረጭት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡

በክልሉ ባሉ 9 ዞኖች ውስጥ የሚገኙ 33 ወረዳዎች የበሽታው ስርጭት መኖሩ ተገልጿል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ÷ እየጨመረ ያለው የወባ በሽታ ስርጭት ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሽታ መከላካል ላይ ያተኮረውን የጤና ኤክስቴንሽ ስራን በማጠናከር የወባና መሰል ተላላፊ በሽታዎች ጫናን ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራም አሳስበዋል፡፡

በማስተዋል አሰፋና በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.