Fana: At a Speed of Life!

መቻልን ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት መላው ህዝብ ተሳታፊ እንዲሆን ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መቻል የስፖርት ክለብን በገንዘብ ለመደገፍ ያለመ ቴሌቶን በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር)ን ጨምሮ የፌደራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የስፖርት ቤተሰቦች ባለሀብቶች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል።

በዚሁ ጊዜ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር)÷ መቻል ለሀገር ባለውለታ የሆነ አንጋፋ ስፖርተኞች ማፍሪያ መሆኑን ጠቅሰው የክለቡን ስምና ዝና ለመመለስ ለሚደረገው ጥረት መላው የሀገሪቱ ህዝብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

መቻል የሰራዊቱ የሞራል ምንጭ የአንጋፋ ስፖርተኞች መፍለቂያ መሆኑን ያወሱት ሚኒስትሯ ክለቡ ሀገራዊ አንድነትንና ሀገራዊ ፍቅርን ማፍራቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

መቻልን ወደ ከፍታ ለመመለስ መሳተፍ ሀገርን መደገፍ ነው ማለታቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.