Fana: At a Speed of Life!

ሰላሟ የበዛና የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በትጋት እንሰራለን-አቶ ብናልፍ አንዱአለም

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላሟ የበዛና የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ዛሬም ነገም በትጋት እና በጋራ እንሰራለን ሲሉ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ተናገሩ፡፡

ዛሬ በሁሉም ሀገሪቱ ክፍል አዲስ አበባን ጨምሮ በ33 የተመረጡ ከተሞች “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ሀገር አቀፍ ሩጫ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሰላም ያለንን ቁርጠኝነት ለመላው አለም አሳይተናል ብለዋል ሚኒስትሩ ።

“ሰላም ለመሆን ብቸኛው እና አማራጭ የሌለው መንገዳችን ሰላም እራሱ በመሆኑ፤ ለሰላም የማንከፍለው መስዋዕትነት እንደሌለ በተግባር ላሳያችሁ ድንቅ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ነው ያሉት።

ሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ለሀገሪቱ ሰላም ያሳዩትን ተነሳሽነትና ቁርጠኝነትም አድንቀዋል፡፡

“ሰላሟ የበዛና የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ዛሬም ነገም በትጋት እና በጋራ እንሰራለን” ብለዋል አቶ ብናልፍ።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.