የመቻል ስፖርት ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቻል ስፖርት ክለብ የገቢ ማሰባሰቢያ (ቴሌቶን) ዛሬ ከምሽቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
መቻል ስፖርት ክለብን ወደ ቀደመ ገናና ስሙ የመመለስና ክለቡን የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ ሲሆን÷ የገቢ ማሰባሰቢያውም የእዚሁ ሥራ አካል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ክለቡን ለማጠናከር እና በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት በሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ሕብረተሰቡ፣ ባለሃብቶች፣ ተቋማት እና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡
ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አካላትም በ 0961910613፣ 0961338325፣ 0961875492፣ 0961940938፣ 0961997624 እና 0961504532 ስልክ ቁጥሮች በመወደወል ማሳወቅ እንደሚችሉ መገለጹን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮቹም÷ 1000603377137 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ 190757676 አቢሲኒያ ባንክ፣ 0579717935011 ዳሽን ባንክ፣ 013071350236800 አዋሽ ባንክ፣ 1042400179571 ኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ 10702376 50215 ስንቄ ባንክ፣ 1724954200001 ኦሮሚያ ባንክ፣ 9900032504845 አማራ ባንክ፣ 00111849630400001 እናት ባንክ እና 1000000894676 መቻል ስፖርት ክለብ መሆናቸው ተብራርቷል፡፡