ሰላምን ዘላቂ በማድረግ የብልጽግና ጉዞን ዳር ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላምን ዘላቂ በማድረግ የተጀመሩ የልማትና የብልጽግና ጉዞዎችን ዳር ማድረስ እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተደድር ኦርዲንበድሪ በድሪ አስታወቁ።
“ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሐሳብ የጎዳና ሩጫ ዛሬ በሐረር ከተማ ተካሂዷል።
በሩጫ ውድድሩ ላይም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ የሐረር ተወላጅ ዳያስፖራ ማሕበረሰብ፣ ሕጻናትና ሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
ርዕሰ መስተደድር ኦርዲን በወቅቱ ባደረጉት ንግግር በትውልድ ቅብብሎሽ የዘለቀውን የክልሉንና የሀገርን ሰላም ማፅናት የሁሉም ኃላፊነት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሰላምን በመጠበቅ እና የሕግ የበላይነትን በማክበር የተጀመረውን የልማትና የብልፅግና ጉዞ ዕውን ማድረግ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡