Fana: At a Speed of Life!

የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዛሬ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መመረቁን ገልጸው፤ ይህ ሆስፒታል ሰፊ መጠነ ርዕይ ያላቸው የህክምና አገልግሎቶች ለመስጠት የተገነባ ነው ብለዋል።

ገና ብዙ ርምጃ መራመድ ቢጠበቅብንም በጤናው ዘርፍ በቂ የህክምና አገልግሎት ለዜጎቻችን ለማቅረብ ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ለዜጎች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በማቅረብ ሥራ ለሚተጉ የጤና ባለሞያዎች ምስጋናችንን እናቀርባለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የጤና ጥበቃ ሥርዓታችንን ለማዘመን በምናደርገው ያላሰለሰ ጥረት ቀጣይ አስተዋፅዖችሁ እና አገልግሎታችሁ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.