Fana: At a Speed of Life!

ለኢነርጂ ዘርፍ የሪፎርም ትግበራ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ተመድቧል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢነርጂ ዘርፍ ሪፎርም፣ ኢንቨንስትመንት እና ሞደርናይዜሽን ፕሮግራም ትግበራ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር መመደቡ ተገለፀ፡፡

በዓለም ባንክ ብድር የሚተገበረው ፕሮግራም ይፋ የተደረገ ሲሆን÷ ፕሮግራሙ ዘርፈ ብዙ የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ያለመ ነው ተብሏል።

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው÷ ለፕሮግራሙ ትግበራ በዓለም ባንክ በኩል 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ተመድቧል ብለዋል።

የኢነርጂ ዘርፍ ልማት በመንግሥት ልዩ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ የተመደበውን መዋዕለ ንዋይ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታዋ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አበበ ዘሪሁን÷ ኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል።

በባንኩ ብድር የሚተገበረው ፕሮግራም ዘርፈ ብዙ የኢነርጂ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር አማካሪ አቶ ጎሳዬ አለማየሁ÷ ፕሮግራሙ የኦፕሬሽን አቅምን እና የሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም ዜጎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

በዓለም ባንክ የሚደገፈውን ይህን ፕሮግራም በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ለማከናወን የታቀደ መሆኑ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.