በሸገር ከተማ የተለያዩ የመሰረት ልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረት ልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው።
በዚህ መሰረትም በከተማ አስተዳደሩ ሰበታ ክ/ከተማ ከ103 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባው ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም በ58 ሚሊየን ብር የተገነቡ ቁጠባ ቤቶች፣ የሆስፒታል ማስፋፊያ፣ የኮብል ስቶን መንገድ እና ፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጀክቶች እንደተመረቁ ተጠቁሟል፡፡
በአጠቃላይ በክፍለ ከተማው በመንግስት በጀትና በባለሃብቶች ተሳትፎ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ፣ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎችና የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።