Fana: At a Speed of Life!

ከለውጡ በኋላ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ከ86 ቢሊየን ዶላር ወደ 205 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) በእጥፍ አድጓል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

በማብራሪያቸውም ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) በእጥፍ ማደጉን አስገንዝበዋል፡፡

እኛ ወደ ቢሮ ስንገባ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) 86 ቢሊየን ዶላር ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ዛሬ ግን 205 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

ከለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ 2ኛ ትልቁ ኢኮኖሚ እንደነበራት አስታውሰው÷ ዛሬ ግን 6ቱ ጎረቤት ሀገራት ተደምረው የእኛን ጂዲፒ አያክሉም ብለዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት የወጪ ንግድ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም ጠቅሰዋል።

በአጠቃላይ ከለውጡ በኋላ 23 ቢሊየን ዶላር ገቢ ከሁሉም ዘርፎች ማመንጨት መቻሉን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ከገቢ ምርቶች በነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ዕዳ ክፍያ አንጻር በዓመት 7 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.