Fana: At a Speed of Life!

የዋጋ ግሽበት ከ30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዋጋ ግሽበት ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማለቱን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት በተከናወኑ ሥራዎች የዋጋ ግሽበት ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ከውጭ ለሚገቡ ምግብ ነክ ቁሶች 10 ቢሊየን ብር በላይ የግብር እፎይታ በመስጠት ወደ ሀገር እንዲገቡ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ምርታማነትን ከማሻሻል ረገድም በዘንድሮው ዓመት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊየን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.