Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 11 ወራት 466 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 11 ወራት 529 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 466 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው ባለፉት 11 ወራት መንግስት 466 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል፡፡

ከወጪ አንጻርም 730 ቢሊየን ብር ለማውጣት ታቅዶ 716 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በገቢ እና ወጪ መካከል ያለው የበጀት ጉድለትም ባለፈው ዓመታት ከነበረበት 4 በመቶ ወደ 2 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት ወጪ ንግድ ከ10 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ገልጸው÷ከሐዋላ አገልግሎትም 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁንም በምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳቢ ሀገር መሆኗን አውስተዋል።

በበጀት ዓመቱም 3 ቢሊየን ዶላር የሚሆን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ስንዴን ጨምሮ በተኪ ምርቶችም ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡

ለአብነትም በበጀት ዓመቱ 2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.