Fana: At a Speed of Life!

አለምአቀፉ የሀረር ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 26ተኛው አለም አቀፍ የሐረር ቀን በሐረር ከተማ ኢማም አህመድ ስታዲየም እየተከበረ ይገኛል፡፡

ቀኑ ባሳለፍነው አመት በካናዳ የተከበረ ሲሆን÷ ዘንድሮ በየአምስት አመቱ ሐረር ከተማ  ላይ ለማድረግ የተገባውን ቃል መሰረት በማድረግ ነው በተለያዩ መርሃግብሮች እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርአቱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች እና የሀረሪ  ክልል ተወላጅ ዳያስፖራዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

26ኛው አለም አቀፍ የሀረር ቀን ከዛሬው የመክፈቻ ስነ ስርአት ጀምሮ በባህል ፌስቲቫል፣ በስፖርት ውድድር፣ በሲምፖዚየም፣ በልማት ፕሮጀክቶች ምረቃና ጉብኝት፣ በአረንጓዴ አሻራ  እና አብሮነትን በሚያጠናክሩ ሁነቶች ለቀጣይ 10 ቀናት ይከበራል ተብሏል፡፡

ቀኑ በተለያየ የዓለም ክፍል ያሉ የሐረሪ ክልል ተወላጆችን ለማቀራረብ ባህል ፣ታሪክ እና ወጋቸውን እንዳይረሱ ለማድረግ በየአመቱ በመሰባሰብ  የሚከበር  ነው።

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.