Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ እንደ ተቋም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እንደ ተቋም በ2016 ዓ.ም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም የማጠቃለያ ግምገማ በፖሊስ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ፣ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ፣ በአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያና በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ እንደ ተቋም በ2016 ዓ.ም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ሲንከባለሉ የመጡ የምርመራ መዝገቦችን በመቀነስ እና የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ የሽብርና ጽንፈኛ ኃይሎች የፈጸሟቸውን ወንጀሎች ተከታተሎ በሙያዊ ብቃት መርምሮ ለሕግ በማቅረብ አመርቂ ሥራዎችን ሠርቷል ብለዋል፡፡

የተቋሙን አመራሮች አቅም በማሳደግ ረገድም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል በውጭና በሀገር ውስጥ የተለያዩ ትምህርትና ስልጠናዎችን ወስዷል ነው ያሉት፡፡

በቴክኖሎጂ አቅምም እንደ ሀገርና እንደ አኅጉር ብዙም ያልተለመዱ የቴክኖሎጂ አቅሞችን ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማምጣት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሀገር አልፎ ለቀጣናው ጭምር ምሳሌ የሚሆን ሥራ እየሠራ ነው ማለታቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.