Fana: At a Speed of Life!

ያሉንን ፀጋ ለይቶ ስራ ዕድል በመፍጠር ከተረጂነት ለመላቀቅ መስራት ያስፈልጋል – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ለዜጎች ክብር! ለዘላቂ ልማት እና ለሀገራዊ ብልፅግና’ በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ÷ ከክልሉ መስረታ በኋላ ባሉት ወራት ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህን ግብ ለማሳካትም ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ዋንኛው ተግባር መሆኑን ገልፀው፤ ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ሲታሰብ ስራ ዕድል መፍጠርና ተደራሽ ማድረግ ወሳኙ ተግባር ነው ብለዋል።

የብዙ ፀጋዎች ባለቤት የሆነው ክልሉ፤ አንዱ ጸፀጋው የሆነውን የሰው ሀይል በአግባቡ ወደስራ በማሰማራት ክልሉን የሰላም የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት ማድረግ ይቻላል ብለዋል።

በተለይ ወጣቶች እንዴት ሰርተን ራሳቸውን መለወጥ እንችላለን በሚል ቁጭት የተለያዩ የስራ ዕድሎችን ላይ በመሰማረት ራሳቸውን ሀገራቸውን ለመቀየር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለሞዴል ለኢንተርፕራይዞቹ ምስጋና አቅርበው መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የ2016 ዓ.ም ክልላዊ የኢንተርፕራይዞች ባዛርና ኤግዚቢሽን በአርባምንጭ ከተማ የከፈቱ ሲሆን÷ በክልሉ ካሉ ዞኖች በተወጣጡ ሞዴል ኢኒተርኘራይዞች የተሰሩ ስራዎች ለእይታ ቀርበዋል።

በታሪክነሽ ሴታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.