Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የክልሉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ በክልል ደረጃ የሚከናወነውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሸበሌ ወረዳ በሚገኘው ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት በመገኘት ዛሬ አስጀምረዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ከርዕሰ መስተዳር ሙስጠፌ መሐመድ በተጨማሪ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣ በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌና የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ በወቅቱ÷ በዘንድሮው መርሃ ግብር በክልሉ 13 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል መታቀዱን ገልጸው፤ እስከ አሁን በችግኝ ጣቢያዎች 9 ሚሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

“በገጠርና በከተሞችም ችግኞችን የመትከል እና የመንከባከብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በተለይም ችግኞችን በቤተሰብ ደረጃ በመትከል ከተሞቻችንን አረንጓዴ ልናደርጋቸው ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሶማሌ ክልል አካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐመድ አደን በበኩላቸው÷ በክልሉ በወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮች 152 ችግኝ ጣቢያዎች ተቋቋመው ችግኞችን በማፍላት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.