Fana: At a Speed of Life!

ለ10 ቀናት የሚቆይ የክትባት ዘመቻ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ቀናት የሚቆይ የክትባት ዘመቻ ይፋ አደረገ፡፡

የክትባት ዘመቻው ክትባት ላልጀመሩ እና ጀምረው ላቋረጡ ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

በዘመቻው ከ1 ሚሊየን በላይ ህፃናት ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸው ተጠቁሟል።

ዘመቻው የሚካሄድባቸው ከ1 ሺህ በላይ ወረዳዎች የተለዩ ሲሆን ለተፈናቃዮች፣ ወረርሽኝ ላለባቸው አካባቢዎች እና ራቅ ላሉ ወረዳዎች ቅድሚያ ይሰጣል ተብሏል።

በትዕግስት አስማማው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.