Fana: At a Speed of Life!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 747 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በክረምት፣ በማታና በርቀት መርሐ ግብር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 747 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል 22ቱ በሶስተኛ ዲግሪ፣ 253 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 1 ሺህ 471 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል አባ ፊጣ (ዶ/ር)÷ ዩኒቨርሲቲው በዚህ አመት የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው መደበኛ ተማሪዎች መካከል 83 በመቶ ፈተናውን ማለፋቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ አየርመንገድና አየር ሃይል ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰው ሃብት ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዘነበወርቅ ገብሬ÷ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡንና የሀገሪቱን ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ተግረዋል።

ተመራቂዎችም ይሄንን አውቀው በቅንነትና በታማኝነት ህዝባቸውን በማገልገል የተጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሙክታር ጣሓ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.