Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 195 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 195 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ 1ሺህ 104 ወንዶች፣ 76 ሴቶችና 15 ጨቅላ ህጻናት ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ ውስጥም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 43 ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተሰራው ሥራ እስካሁን ከ54 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.