Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዋርሶ ከተማ ቀጥታ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ፖላንድ መዲና ዋርሶ ቀጥታ በረራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በሳምንት 4 ጊዜ የሚደረገው በረራው÷አየር መንገዱ በአውሮፓ ያለውን መዳረሻ ወደ 24 ከፍ እንደሚያደርገው ተመላክቷል፡፡

የቀጥታ በረራው የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተገልጿል፡፡

የሀገራቱን ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማሳደግ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማሳደግ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተጠቁሟል፡፡

በቤቴልሄም መኳንት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.